
ደብረ ብርሃን: ጥር 8/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የደብረ ብርሃን ከተማ ባሕል እና ስፖርት ተጠሪ ጽሕፈት ቤት የሆቴል እና ሬስቱራንት ብቃት ማረጋገጥ ባለሙያ ብስራት ታደለ እንዳሉት የከተራ እና የጥምቀት በዓል ባሕላዊ እሴታቸውን ጠብቀው እንዲከበሩ ከአጋር አካላት ጋር በመቀናጀት የቅድመ ዝግጅት ሥራ እየተሠራ ነው።
የከተራ እና የጥምቀት በዓላት በወቅታዊ ችግር ምክንያት የተቀዛቀዘውን የቱሪዝም ዘርፍ ለማነቃቃት እድል እንደሚፈጥርም ነው ባለሙያው ያብራሩት፡፡
አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ተገቢዉን አገልግሎት እንዲሰጡ መግባባት ላይ መደረሱንም አንስተዋል፡፡
በዓሉ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን እና ትውፊቱን በጠበቀ መልኩ እንዲከበር ለማስቻል ሁሉም ባለድርሻ አካላት ለተግባራዊነቱ እንዲሠሩ ባለሙያው አሳስበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ወንድይፍራው ዘውዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!