የከባድ ተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ሰዓት ማሻሻያ ተደረገበት፡፡

133

ባሕር ዳር፡ የካቲት 19/2012 ዓ.ም (አብመድ) የትራፊክ መጨናነቅ ችግሩን ለማቃለል በአዲስ አበባ የከባድ ተሸከርካሪዎች እንቅስቃሴ ላይ የሰዓት ማሻሻያ ተደርጓል፡፡

በዚህም መሠረት ከባድ ተሽከርካሪዎች ጠዋት ከ1፡00 እስከ 3፡00 እና ከሰዓት ከ 10:30 እስከ12:00 ውጪ ባሉ ሰዓታት እንዲንቀሳቀሱ ተወስኗል።

ማሻሻያው የተደረገው የተለያዩ ተቋማት በሰዓት ገደቡ ምክንያት በተለይም የግንባታ ስራዎቻቸውን ለማከናወን እንደተቸገሩ ቅሬታ በማቅረባቸው ነው ብሏል ከተማ አስተዳደሩ፡፡ በመሆኑም ለትራፊክ እንቅስቃሴው ጫና በማይፈጥር መልኩ ማሻሻያው ተደርጓል ነው የተባለው።

እስካሁን በነበረው ህግ በከተማዋ የሚገኙ ከባድ ተሽከርካሪዎች ከጠዋቱ 4፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ ብቻ መንቀሳቀስ ይፈቀድላቸው እንደነበር ይታወሳል፡፡

Previous articleየፖሊሲ እና የመተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ ማድረጉን አብን አስታወቀ፡፡
Next articleበኩር ጋዜጣ የካቲት 23/2012 ዓ/ም ዕትም