
ባሕር ዳር: ጥር 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በመድረኩ የምሥራቅ እዝ አዛዥና የጎጃም ኮማንድ ፖስት ሰብሳቢ ሌተናል ጀኔራል መሐመድ ተሰማ፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ክላስተር አስተባባሪና የግብርና ቢሮ ኃላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)፣ የደብረማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ መንበሩ ዘውዴን ጨምሮ ሌሎች የክልል ከፍተኛ መሪዎችና የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ መኮንኖች እንዲሁም የከተማ አሥተዳድሩ ጠቅላላ አመራር በመድረኩ ተሳትፈዋል።
በውይይቱም የከተማው የሰላም ኹኔታ፣ ሕግ የማስከበርና የልማት ሥራዎች ያሉበትን ኹኔታ በዝርዝር በመገምገም በቀጣይ ሰላማችን ዘላቂና ዋስትና እንዲኖረው፤ የሕግ የበላይነት እውን እንዲኾን እንዲሁም የልማት ሥራዎችን ለማስቀጠል በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ውይይት ተካሂዷል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!