
ባሕር ዳር፡ ጥር 07/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት “ቱሪዝም ከአምስቱ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ምሰሶዎች አንዱ እንደመኾኑ መጠን የግሉ ዘርፍ ወሳኝ ሚና እንዳለው እንገነዘባለን” ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው በዘርፉ የሚደረጉ የገበታ ለሸገር፣ ገበታ ለሀገር እና ገበታ ለትውልድ ሥራዎች የግሉ ዘርፍ መዳረሻዎችን እና አገልግሎቶችን በይበልጥ እንዲሰማራ መንገድ ለመክፈት ታልመው የተሠሩ ናቸው ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!