የክልሉ የመንግሥት ሠራተኞች ያጋጠመውን የጸጥታ ችግር ተቋቁመው በተገቢው መንገድ መሥራት መቻላቸውን የክልሉ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ኮሚሽን ገለጸ፡፡

11

ጎንደር: ጥር 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ኮሚሽን የ2016 በጀት ዓመት የስድስት ወር የእቅድ አፈጻጸሙን ከተቋሙ የጎንደር ቀጣና የሥራ ኀላፊዎች እና ባለሙያዎች ጋር በጎንደር ከተማ ገምግሟል።

የክልሉ ሲቪል ሰርቪስ እና ሰው ሀብት ልማት ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ካሣ አበባው በክልሉ የሚገኙ የመንግሥት ሠራተኞች ማኅበረሰቡን በማገልገል ረገድ በባለፉት ስድስት ወራት በችግር ውሰጥም ቢኾን ሥራዎችን በተገቢው መንገድ ሲሠሩ እንደነበር አንስተዋል፡፡

በክልሉ የሚገኙ ተቋማት ከባለፈው ስድስት ወር አፈጻጸማቸው በተሻለ መንገድ ለሕዝቡ አገልግሎት ለመስጠት መሥራት እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡ ምክትል ኮሚሽነሯ በክልሉ ያለውን አመራር እና ባለሙያ በየደረጃው በማሠልጠን ኀላፊነታቸውን እንዲወጡ ማድረግ የቀጣይ ተግባር ይኾናል ብለዋል።

አስተያየታቸውን ለአሚኮ የሰጡን ተሳታፊዎችም በነበረው የጸጥታ ችግር ውስጥም ቢኾን ማኅበረሰቡ አገልግሎት እንዲያገኝ ይደረግ እንደነበር ገልጸዋል፡፡ እስካሁን የነበረውን አሠራር በማስቀጠል ማኅበረሰቡ የሚያነሳቸው የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮችን ለማስተካከል እንደሚሠሩም አረጋግጠዋል።

ዘጋቢ፡- ደስታ ካሳ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበሰሜኑ ጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው የጤና ተቋማት ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ።
Next article“ቱሪዝም ከአምስቱ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ምሰሶዎች አንዱ እንደመኾኑ መጠን የግሉ ዘርፍ ወሳኝ ሚና እንዳለው እንገነዘባለን” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)