በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት ለደረሰባቸው የጤና ተቋማት ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ተደረገ።

9

ደሴ: ጥር 6/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማኅበር ከአማራ ክልል ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር በደቡብ ወሎ እና በሰሜን ወሎ ዞኖች ለሚገኙ ጤና ጣቢያዎች እና ጤና ኬላዎች የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል።

የኢትዮጵያ ጤና አጠባበቅ ማኅበር ዳይሬክተር ዶክተር ዓለማየሁ መኮነን ድጋፉ በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት የደረሰባቸውን ጤና ተቋማት መልሶ ለማቋቋም የተደረገ መኾኑን ገልጸዋል፡፡
ከዚህ በፊት በአማራ ክልል እና በትግራይ ክልል ለሚገኙ ጤና ተቋማት ተመሳሳይ ድጋፍ ማድረጋቸውን አብራርተዋል።

ዳይሬክተሩ በሁለቱ ዞኖች ለሚገኙ እና በጥናት ለተለዩ የጤና ተቋማት እና ጤና ኬላዎች ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ በማድረግ የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸውን አስረድተዋል፡፡ በቀጣይም ድጋፉን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ አስገንዝበዋል።

ዘጋቢ፡- ማህሌት ተፈራ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከ6 ሺህ በላይ በምገባ መርሐ ግብር መታቀፍ ያለባቸው ተማሪዎች መለየቱን የደሴ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።
Next articleየክልሉ የመንግሥት ሠራተኞች ያጋጠመውን የጸጥታ ችግር ተቋቁመው በተገቢው መንገድ መሥራት መቻላቸውን የክልሉ ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ኮሚሽን ገለጸ፡፡