የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ሠራተኞች በሳይንስ ሙዚየም የተከፈተውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዲፕሎማሲ ሳምንት አውደ ርዕይን ጎበኙ።

53

አዲስ አበባ: ጥር 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ) “ዲፕሎማሲያችን ለብሔራዊ ጥቅማችን” በሚል መሪ መልእክት ለሦስት ሳምንታት የሚቆየው አውደ ርዕይ በፕሬዚደንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ ባሳለፍነው ሳምንት መከፈቱ ይታወሳል።

ኢትዮጵያ ከአፍሪካ መዲና እስከ ዓለም መድረክ ለ3 ሺህ ዓመታት ያለፈችባቸውን የውጭ ግንኙነት እና የዲፕሎማሲ መንገዶች የሚያሳየውን አውደ ርዕይ የአሚኮ አዲስ አበባ ቅርንጫፍ ጋዜጠኞች እና አመራሮች ጎብኝተዋል።

በጉብኝቱ ላይ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባለሙያዎች ከ100 ዓመት በላይ በተሻገረው የውጭ ግንኙነት ሥራ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ እስከ ዓለም መድረክ የነበራትን ሁለንተናዊ እንቅስቃሴ ለአሚኮ ጋዜጠኞች ገለጻ አድርገዋል።

ዘጋቢ፡- ድልነሳ መንግሥቴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየኮንትራት ቅጥር ማስታወቂያ
Next articleከ6 ሺህ በላይ በምገባ መርሐ ግብር መታቀፍ ያለባቸው ተማሪዎች መለየቱን የደሴ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ።