እስከ ጥር 17 የሚቆየው የአፍሪካ ኅብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ ስብሰባ በአዲስ አበባ ተጀመረ።

53

ባሕር ዳር: ጥር 06/2016 ዓ.ም (አሚኮ) 47ኛው የአፍሪካ ኅብረት የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ ስብስባ ዛሬ በኅብረቱ ዋና መቀመጫ አዲስ አበባ ተጀምሯል።

ስብሰባው “ለ21ኛው ክፍለ ዘመን የሚመጥን አፍሪካዊ ማስተማር፤ የማይበገሩ የትምህርት ሥርዓቶች በመገንባት በአፍሪካ ሁሉን አቀፍ የሕይወት ዘመን፣ ጥራትና አግባብነት ያለው የትምህርት ተደራሽነትን ማስፋት“ በሚል መሪ ሀሳብ የሚካሄድ ነው።

በስብሰባው ላይ የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት እና የኅብረቱ መሪዎች፣ የኮሚቴው ሰብሳቢ እና የኅብረቱ አባል ሀገራት አምባሳደሮች እየተሳተፉ ነው።

ስብስባው የካቲት 5 እና 6 ቀን 2016 ዓ.ም ለሚካሄደው 44ኛው የአፍሪካ ኅብረት የሥራ አስፈጻሚ ምክር ቤት ስብስባ እንዲሁም የካቲት 9 እና 10 ቀን 2016 ዓ.ም ለሚከናወነው 37ኛው የኅብረቱ የመሪዎች ጉባኤ የሚቀርቡ ረቂቅ አጀንዳዎች ላይ ይወያያል ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢዜአ ዘግቧል።

በተጨማሪም ኮሚቴው በአፍሪካ ኅብረት ስር የሚገኙ የተለያዩ ተቋማት የአፈጻጸም እንዲሁም ኅብረቱ እንደ አውሮፓውያኑ የዘመን አቆጣጠር በ2023 ያካሄዳቸውን ስብስባዎች የተመለከቱ ሪፖርቶችን ያደምጣል። የኅብረቱ የቋሚ ተወካዮች ኮሚቴ ስብሰባ እስከ ጥር 17 ቀን 2016 ዓ.ም ይቆያል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጦርነት የሀገርን ኢኮኖሚ ከማድቀቁም በላይ በሴቶች እና ሕጻናት ላይ የሚያደርሰው ጉዳት የከፋ እንደኾነ የዝቋላ ወረዳ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡
Next articleለስጋ ደዌ በሽታ ተገቢውን ትኩረት በመስጠት ማጥፋት እንደሚገባ የአማራ ክልል ሴቶች ሕጻናት እና ማኅበረዊ ጉዳይ ቢሮ አሳሰበ።