የአማራ ክልል ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ ከዩኒቨርሲቲዎች ጋር ያደረገውን የጥናት ሰነድ ማስረከቡን አስታወቀ፡፡

31

ባሕር ዳር: ጥር 6/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የአማራ ክልል ማዕድን ሃብት ልማት ቢሮ ከባሕር ዳር፣ ከጎንደር፣ ከወሎ፣ ከወልድያ እና ከደብረ ብርሐን ዩኒቨርሲቲዎች ጋር የሥነ ምድር ጥናት እና ካርታ ሥራ አድርጓል።

በተጨማሪሞ ቢሮው በከፍተኛ መስፈርት የማዕድን ፍለጋ፣ ክምችት፣ ስርጭት እና ጥራትን የሚያመለክቱ የተጠኑ ጥናቶች የሰነድ ርክክብ አድርጓል።

የቢሮው ምክትል ቢሮ ኀላፊ ታምራት ደምሴ በሰነድ ርክክቡ ላይ ጥናቱን ያደረጉ ዩኒቨርሲቲዎችን እና ምሁራንን አመሥግነዋል።

በቀጣይም በትብብር በመሥራት የሥራ ዕድል መፍጠር፣ ዜጎችን ከድህነት ማውጣት እና የክልሉን ምጣኔ ሃብትም ለማሳደግ እንደሚያስችል ገልጸዋል።

ዘጋቢ፡- ዋሴ ባየ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበኩር ጋዜጣ ጥር 06/2016 ዓ.ም ዕትም
Next articleጦርነት የሀገርን ኢኮኖሚ ከማድቀቁም በላይ በሴቶች እና ሕጻናት ላይ የሚያደርሰው ጉዳት የከፋ እንደኾነ የዝቋላ ወረዳ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡