
ባሕር ዳር: ጥር 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ እንዳሉት ከምንም በላይ ሕግ እና ሥርዓትን በማስከበር የሕዝብን ደኅንነት እና ሰላም ለማረጋገጥ ኅብረተሰቡ ያሳየው ከፍተኛ ድጋፍ እና አስተዋይነት የክልሉ ሕዝብ ለሰላም ያለውን ቀናኢነት ማሳያ ነው፡፡
ክልሉ የሚጸናው፣ የሚያድገው እና የሚበለጽገው ሁሉም ለሰላም በሚሰጠው ከፍ ያለ ትርጉም እና ሕዝቦች በሚያደርጉት የጋራ ርብርብ ነው ብለዋል ርእሰ መሥተዳድሩ፡፡ ዋነኛዉ የሰላም አቅማችን ሕዝባችን ነውም ብለዋል፡፡
ከእኛም አኳያ የሕዝባችንን ፍላጎት ለማሟላት እስከጠቀመ ድረስ በየትኛዉም ጊዜና አጋጣሚ የሚመክረን ካለ ለማዳመጥ ዝግጁ ነን፤ ምክንያቱም እኛም እንደ አመራር የተለየ ፍላጎት የለንም ነው ያሉት፡፡ ዓላማችን ሰላምን የማስፈን የሕግ የበላይነትን የማረጋገጥ ጉዳይ ብቻ ነው ብለዋል፡፡
ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የአማራ ክልልን ሕዝብ እወዳለሁ የሚል ሁሉ ለክልሉ ዘላቂ ሰላም ዘብ ይቁም ብለዋል በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባጋሩት መልእክት።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!