የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ለታማኝ ግብር ከፋዮች ዕውቅና እና ሽልማት ሰጠ።

16

አዲስ አበባ: ጥር 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር “ግብር ለሀገር ክብር” በሚል መሪ መልእክት ለ562 ታማኝ ግብር ከፍዮች ዕውቅና እና ሽልማት ሰጥቷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ገቢዎች ቢሮ ኀላፊ አደም ኑሬ በ2015 በጀት ዓመት 107 ቢሊዮን ብር ገቢ ለመሰብሰብ ታቅዶ 109 ቢሊዮን ብር መሠብሠብ ተችሏል ብለዋል።

የከተማ አሥተዳደሩ ለአምስተኛ ግዜ እያካሄደ ባለው የታማኝ ግብር ከፍዮች ዕውቅና እና ሽልማት የመስጠት መርሐ ግብር 562 ግብር ከፋዮች የተቀመጡትን መስፈርቶች አሟልተው ለዚህ ሽልማት እንደበቁ ተናግረዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ያለግብር ሀገር እንደማትለማ ገልጸው በታማኝነት ግዴታቸውን የተወጡ ታማኝ ግብር ከፋዮችን አመሥግነዋል።

ሕግና ሥርዓትን ተከትለው የማይሠሩ ተቋማት እና ብልሹ አሠራርን የሚከተሉ ባለሙያዎች ላይም ሕጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ገልጸዋል።

ዘጋቢ፦ ቤተልሄም ሰለሞን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የአማራ ክልል ሕዝብና መንግሥት የሰጠንን ኀላፊነት ለመወጣት ቁርጠኛ ኾነን ልንሠራ ይገባል” አህመዲን መሀመድ (ዶ.ር)
Next article“የሕዝባችንን ፍላጎት ለማሟላት እስከጠቀመ ድረስ በየትኛዉም ጊዜና አጋጣሚ የሚመክረን ካለ ለማዳመጥ ዝግጁ ነን” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ