“የአማራ ክልል ሕዝብና መንግሥት የሰጠንን ኀላፊነት ለመወጣት ቁርጠኛ ኾነን ልንሠራ ይገባል” አህመዲን መሀመድ (ዶ.ር)

43

ደብረ ብርሃን: ጥር 05/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በምክትል ርእሰ መሥተዳደር ማዕረግ የከተሞች ልማት ዘርፍ አስተባባሪና የከተማና መሰረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አህመዲን መሀመድ (ዶ.ር) በደብረብርሃን ከተማ በተጀመረው የአመራሮች ሥልጠና ላይ ተገኝተው “የአማራ ክልል ሕዝብና መንግሥት የሰጠንን ኀላፊነት ለመወጣት ቁርጠኛ ኾነን ልንሠራ ይገባናል” ብለዋል።

“ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ መልእክት ከሰሜን ሸዋ ዞን፣ ከደብረብርሃን ከተማ አሥተዳደር እና ከኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ለተወጣጡ የሥራ ኀላፊዎች እና የፀጥታ አካላት ሥልጠና መስጠት ተጀምሯል።
ዶክተር አህመዲን በክልሉ በነበረው የሰላም እጦት በርካታ ችግሮች ነበሩ ብለዋል።

ችግሮቹን በዘላቂነት ለማስተካከል በቁርጠኝነት መሥራት እና መታገል እንደሚገባም አሳስበዋል።

በመድረኩ የኮማንዶና አየርወለድ ዋና አዛዥ እና የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት አስተባባሪ ሌተናል ጄኔራል ሹማ አብደታን ጨምሮ ከሰሜን ሸዋ ዞን፣ ከደብረብርሃን ከተማ አሥተዳደር እና ከኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር የተውጣጡ የፀጥታ ኀይል አባላት እና አመራሮች ተገኝተዋል።

ዘጋቢ፦ ኤልያስ ፈጠነ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ግጭት በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሀገራዊ ምክክር ሂደቶችን ለማከናወን ዝግጅት እየተደረገ ነው” ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ
Next articleየአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ለታማኝ ግብር ከፋዮች ዕውቅና እና ሽልማት ሰጠ።