
ባሕር ዳር፡ ጥር 04/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የዲፕሎማሲ ሳምንት አካል የሆነው የአምባሳደሮች ስብሰባ ዛሬ መካሄድ ጀምሯል።
ስብሰባውን ያስጀመሩት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ናቸው።
በዚህም በመድረኩ የዲፕሎማሲ ስራዎችን አፈጻጸም አንስተዋል።
የአምባሳደሮች አመታዊ ስብሰባ ከዛሬ ጥር 4 ጀምሮ እስከ ጥር 18 ቀን 2016ዓ.ም እንደሚቀጥል ነው የተገለጸው።
ፋና እንደዘገበው፤ በእነዚህ ቀናቶችም ከአመታዊ ስብሰባው ጎን ለጎን የመስክ ጉብኝት እንደሚኖር ተመላክቷል።
በተጨማሪም የሩብ አመቱ አፈጻጸም ሪፖርት እንደሚቀርብ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም (ዶ.ር) ገልጸዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!