
አዲስ አበባ: ጥር 03/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ለሀገረ መንግሥት ግንባታ የወጣት ምሁራን ሚና በሚል መሪ ሃሳብ በአዲስ አበባ ውይይት እየተካሄደ ነው።
በብልጽግና ፓርቲ ወጣቶች ሊግ ዋና ጽሕፈት ቤት አዘጋጅነት እየተካሄደ ባለው መድረክ የወጣቶች ሊግ ማኅበራት ፕሬዚዳንቶች፣ የዩኒቨርሲቲ ምሁራን፣ አዛውንቶች እና ወጣቶች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በመድረኩ የተገኙት ምሁራን እንዳሉት በሀገረ መንግሥት ግንባታ የወጣቶች ሚና ከፍተኛ ነው። ወጣትነት ለነገዉ ትውልድ ምን ዓይነት ሀገር ማስረከብ እንዳለብን የምንወስንበት ወሳኝ ጊዜ በመኾኑ ለታሪክ ተወቃሽ እንዳንኾን በአስተውሎት ልንራመድ ይገባል ብለዋል።
ብዙ መልካም የጋራ ትናንቶችን በማሳደግ የጋራ ነጋችንን ልንገነባ ይገባል ያሉት ምሁራኑ ይሄን ለማሳካት ደግሞ የሕዝባችንን መልካም እሴቶች መፈለግ እና ማጎልበት ይገባል ብለዋል።
በመድረኩ ተጋባዥ እንግዶች በሰጡት ሃሳብ እኛ አባቶች በምግባር ብንወድቅ እንኳ እናንተ ልትወድቁ አይገባም፡፡ ችግር ሲፈጠር ወጣቶች የመፍትሔ አካል በመኾን ኀላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።
ዘጋቢ፡- በለጠ ታረቀኝ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!