“የዲፕሎማሲያችን” አውደ ርዕይ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት እየተካሄደ ነው፡፡

19

ባሕር ዳር: ጥር 02/2016 ዓ.ም (አሚኮ) “የዲፕሎማሲያችን” አውደ ርዕይ “ ዲፖሎማሲያችን ለብሔራዊ ጥቅማችን” በሚል መሪ ሀሳብ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው፡፡

በመክፈቻ ሥነ ሥርዓቱ ፕሬዚዳንት ሣኅለወርቅ ዘውዴን ጨምሮ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን፣ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር እና ሌሎችም ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች፣ ዲፕሎማቶች እና ሌሎች ጥሪ የተረደገላቸው እንዶች ተገኝተዋል፡፡

ኢትዮጵያ በታሪክ ከበርካታ ሀገራት ጋር ጥብቅ ወዳጅነትን የመሠረተች፣ ለፍትሕ እና ለእኩልነት የቆመች፣ የራሷን ነጻነት አስጠብቃ የአፍሪካውያን ነጻነት እንዲጠበቅ ብርቱ ትግል ያደረገች ሀገር ናት፡፡

ኢትዮጵያ ለዘመናት በዘለቀው የዲፕሎማሲ ሥራዋ የጋራ ተጠቃሚነትን እና ፍትሐዊነትን መርኋ አድርጋ የዘለቀች ሀገር እንደኾነች ይነገራል፡፡

የአፍሪካ ኅብረትን በመመስረት አፍሪካውያንን ያሰባሰበች፣ ለአፍሪካዊ ችግር አፍሪካዊ መፍትሔን ያፈላለገች፣ ለጥቁር መብት የተከራከረች የአፍሪካውያን ምልክት እና የነጻነት አርማ የኾነች ሀገርም ናት ኢትዮጵያ፡፡

ዓለም የደረሰበትን ዲፕሎማሲ በመጠቀም ብሔራዊ ጥቅሞቿን ለማስከበር እየሠራች ነው፡፡ ለዚህም ይኾን ዘንድ የድፕሎማሲ አውደ ርዕይ ክፍት አድርጋለች ተብሏል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article675 ተጠርጣሪዎችን በሦስት ዙር የተሃድሶ ሥልጠና በመስጠት ወደ ኅብረተሰቡ መቀላቀሉን የባሕር ዳር ኮማንድ ፖስት አስታወቀ።
Next articleከአፍሪካ መዲና እስከ ዓለም መድረክ ድረስ” የተሰኘ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የዲፕሎማሲ ፎረም ተከፈተ።