በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች የተቀናጀ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃ ሥራ የተሻለ ተሞክሮ እንዳለ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ ገለጹ፡፡

32

ደሴ: ጥር 1/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የተቀናጀ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃ ሥራ የተሻለ ተሞክሮ እንዳለ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ ገልጸዋል፡፡

የ2016 ዓ.ም የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃ ሥራ በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ ሂተቻ ቀበሌ ተጀምሯል፡፡ በተቀናጀ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃ ሥራ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር ላይ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳህሉን (ዶ.ር) ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል ።

በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አስተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር) በዘንድሮው የተፋሰስ ሥራ በክልሉ ከ9 ሺህ በላይ ተፋሰሶች ላይ የአፈር እና ውኃ ጥበቃ ሥራ ይከናወናል ብለዋል።

የተቀናጀ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃ ሥራ ለግብርና ልማት አስፈላጊ በመኾኑ በልዩ ትኩረት እንደሚሠራ የገለጹት ዶክተር ድረስ ሰላምን እያስጠበቅን የተፈጥሮ ሃብት ሥራችንን አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል፡፡

የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ በአማራ ክልል በተለያዩ አካባቢዎች የተቀናጀ የተፈጥሮ ሃብት ልማት ጥበቃ ሥራ የተሻለ ተሞክሮ እንዳለ ገልጸዋል። ይህንኑ አጠናክሮ ማስቀጠል ተገቢ እንደኾነም አቶ ይርጋ ተናግረዋል።

ዘጋቢ፡- ከድር አሊ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleሕዝብ በጊዜያዊ ችግሮች ሳይሰናከል ባሕሉን በመጠቀም አካባቢው ወደ ቀድሞ ሰላሙ እንዲመለስ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ተጠየቀ፡፡
Next article“የክልሉ መንግሥት የሰብዓዊ አያያዝ ላይ በከፍተኛ ጥንቃቄ ሠርቷል” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ