
ከሚሴ: ታኅሳስ 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ውይይት እየተካሄደ ነው፡፡
በውይይቱ ላይ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን እና የክልሉ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኀላፊ አቶ እንድሪስ አብዱ በኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር በከሚሴ ከተማ ተገኝተው ከዞን ከፍተኛ አመራሮች እና ከፀጥታ ተቋማት ኀላፊዎች ጋር ምክክር አደርገዋል።
በውይይቱ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳደር አብዱ ሁሴን “በብሔረሰብ አሥተዳደሩ እየተሠራ ያለው የሕግ ማስከበር ተግባር የሚበረታታ ነው” ብለዋል። በቀጣይም ዘላቂ እና አስተማማኝ ሰላም ለመገንባት፤ በውስጥም በውጭም ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በጋራ መታገል እንደሚገባ አቅጣጫ አስቀምጠዋል።
በውይይት መድረኩ ላይ የአካባቢውን አንጻራዊ ሰላም አበረታች ነው ተብሏል። የተገኘውን አንጻራዊ ሰላም ዘላቂነት ለማረጋገጥ አሁንም ሥራዎች መሠራት እንዳለባቸው በውይይቱ ተነስቷል።
ዘጋቢ:- ይማም ኢብራሂም
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!