“የልብ ህሙማን ህፃናት ወር” ተብሎ በተሰየመው የጥር ወር ኢትዩ ቴሌኮም የተለያዩ የገቢ ማሰባሰቢያ ሥራዎችን አንደሚያከናውን አስታወቀ።

41

አዲስ አበባ: ታኅሳሥ 30/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በዚህ የድጋፍ መርሐ ግብር የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች የኢትዮ ቴሌኮም እና የቴሌብርን የማኅበራዊ ሚዲያ በመከተል እና በየቀኑ የሚለቀቁ ይዘቶችን ለሌሎች በማጋራት ብቻ ምንም ዓይነት ወጪ ሳያወጡ ድጋፍ ማድረግ የሚችሉበት አሠራር ተዘርግቷል ተብሏል።

ኢትዮ ቴሌኮም በቋሚነት ለማዕከሉ የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ መቆየቱን የገለፁት በኢትዮ ቴሌኮም የኮምዩኒኬሽን ዲቪዢን ዳይሬክተር አዜብ መለሰ የጥር ወርን በተለየ ኹኔታ የልብ ህሙማን ህፃናት ወር ብሎ በመሰየም የዘመቻ ድጋፍን እንደሚያደረግ ተናግረዋል።

የየኢትዮጵያ የልብ ህሙማን መርጃ ማዕከል ሜዲካል ዳይሬክተር ሜክሎል መንግሥቱ ማዕከሉ በየጊዜው የሚያጋጥሙትን የአላቂ እቃዎች ችግር ለመፍታት የኢትዮ ቴሌኮም ድጋፍ አጋዥ ይኾናል ብለዋል። የድጋፍ ዘመቻው ከነገ ጀምሮ በይፍ እንደሚጀመርም ተገልጿል።

ዘጋቢ፦ ቤተልሄም ሰለሞን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበአማራ ክልል 61 የአስፓልት መንገድ ፕሮጀክቶች እየተሠሩ መኾኑን የኢትዮጵያ መንገዶች አሥተዳደር አስታወቀ፡፡
Next articleበ30 ሚሊየን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ የከተማ መሬት አያያዝ እና ማዘመን ተግባር ሊከናወን መኾኑ ተገለጸ።