“የልደት በዓል በመላው ክልላችን በድምቀት ተከብሮ እንዲጠናቀቅ ላደረጋችሁ በሙሉ ልባዊ ምሥጋናዬን ለማቅረብ እወዳለሁ” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ

18

ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ባስተላለፉት መልእክት የልደት በዓል በመላው ክልላችን በድምቀት ተከብሮ እንዲጠናቀቅ፤ በተለይም ደግሞ በታሪካዊቷ እና በደማቋ ላሊበላ ከተማ ያለምንም ችግር እንዲከበር ላደረጋችሁ በሙሉ ልባዊ ምሥጋናዬን በራሴ እና በክልሉ መንግሥት ስም ለማቅረብ እወዳለሁ ብለዋል፡፡

ማኅበራዊ ሀብቶቻችን እና ባሕላዊ እሴቶቻችን ለአንድነታችን እና ለጸና መግባባታችን እውንነት ሁነኛ አጋዥ መሳሪያዎች ይሆኑ ዘንድ ሕዝባችን በየአጋጣሚዎቹ ሁሉ የበኩሉን አስተዋጽዖ እያደረገ ስለመሆኑ በውል ለመረዳት ችያለሁ ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ። ለዚህ ገደብ የለሸ አስተዋጽዖም ከልቤ ለማድነቅ እና ለማመሥገን እወዳለሁ ብለዋል።

ገናን በቅዱስ ላሊበላ እንዳከበርነዉ ሁሉ በቀጣይም በክልላችን በሚከበሩ ሌሎች ሃይማኖታዊ እና ባሕላዊ ክብረ በዓላት ላይ ቱሪስቶች እንዲገኙ እና በእነዚህ በድንቅ ምድር አማራ ውስጥ በድምቀት በሚከበሩ ኩነቶች ላይ ታዳሚ እንዲኾኑ እጋብዛለሁ ብለዋል። መላው ሕዝባችንም በዓላቱ በሰላም ይከበሩ ዘንድ ለሚያደርገው አስተዋጽዖ ከወዲሁ ለማመሥገን እወዳለሁ ነው ያሉት በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባጋሩት መልእክት።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከሶማሌላንድ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጋር ተወያዩ።
Next article“ግብርና የልማት እና የእድገት የጀርባ አጥንት በመኾኑ ሰላም ይፈልጋል” ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)