
ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከሶማሌላንድ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሜጄር ጄኔራል ኑህ ኢስማኤል ታኒ ጋር በወታደራዊ ትብብር ዙሪያ ተወያይተዋል።
በሶማሊላንድ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሜጄር ጄኔራል ኑህ ኢስማኤል ታኒ የተመራ ልዑክ በመከላከያ ጠቅላይ መምሪያ ሲደርስ በጄኔራል መኮንኖች አቀባበል ተደርጎለታል።
የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላና የሶማሊላንድ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ሜጄር ጄኔራል ኑህ ኢስማኤል ታኒ በወታደራዊ ትብብር ዙሪያ አብረው ለመሥራት የሚያስችላቸውን ውይይት አድርገዋል።
በቅርቡ የሶማሌላንድ ፕሬዘዳንት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ጋር መወያየታቸውና የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወሳል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!