በክልሉ በተፈጠረው የሰላም ችግር በቱሪዝም እንቅስቃሴው ላይ ጉዳት መድረሱን የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አቶ አራጌ ይመር ገልጸዋል፡፡

32

ባሕርዳር: ታኅሳሥ 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በክልሉ በተፈጠረው የሰላም ችግር በቱሪዝም እንቅስቃሴው ላይ ጉዳት መድረሱን የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አቶ አራጌ ይመር ገልጸዋል፡፡ ዋና አሥተዳዳሪው እንዳሉት የላሊበላ ከተማ በዩኔስኮ የተመዘገቡ የቅርሶች መገኛ መኾኗ ለሀገራችን ምጣኔ ሃብታዊ እና ማኅበራዊ መስተጋባር ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላት ከተማ አድርጓታል።

ዋና አስተዳዳሪው “ላሊበላ ኢትዮጵያውያንን በእምነት እና በባሕል ያስተሳሰረ፣ ለሀገሪቱ የቱሪዘም ዘርፍም ከፍተኛ አቅም የፈጠረ ቅርስ ነው” ብለዋል። ቅርሱ በተለይም የሥራ እድል በመፍጠር እና ኢኮኖሚያዊ አቅምን በማጎልበት ፋይዳው ከፍተኛ መኾኑን አንስተዋል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል እና የቅዱስ ላሊበላ ልደት በጥምረት የሚከበሩ መኾኑ ላሊበላን ልዩ ያደርገዋል ነው ያሉት፡፡

ይሁን እንጅ ባለፉት ወራት በክልሉ የተፈጠረው የሰላም እጦት ችግር በአካባቢው የቱሪዝም እንቅስቃሴ ላይ ጉዳት አድርሷል፣ ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ውድመትም ደርሷ ነው ያሉት፡፡ የላሊበላ ከተማን የቱሪዝም እንቅስቃሴ ወደ ነበረበት ለመመለስ መንግሥት ከሃይማኖት አባቶች እና ከሀገር ሽማግሌዎች ጋር በመቀናጅት በሠራው ሰፊ ሥራ በዓሉን በዚህ መልኩ ማክበበር ተችለዋል ብለዋል። አኹን የተፈጠረውን ሰላም በዘላቂነት ለማረጋገጥ ማኅበረሰቡ ኃላፊነቱን እንዲወጣም ዋና አስተዳዳሪው ጠይቀዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“አፈርን በኮምፖስት የማበልፀግ ልምምዳችንን በተሻለ ሁኔታ ካዳበርን ሰፊ ጥቅም ልናገኝበት እንችላለን” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
Next articleማኅበረ ቅዱሳን በደቡብ ወሎ ዞን ጃሪ ለሚገኙ ተፈናቃዮች የእርድ እንስሳትን ድጋፍ አደረገ፡፡