“አፈርን በኮምፖስት የማበልፀግ ልምምዳችንን በተሻለ ሁኔታ ካዳበርን ሰፊ ጥቅም ልናገኝበት እንችላለን” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

12

ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) አፈርን በኮምፖስት የማበልፀግ ልምምዳችንን በተሻለ ሁኔታ ካዳበርን ሰፊ ጥቅም ልናገኝበት እንችላለን ብለዋል።

በተለይም በከተማ ግብርና ስራችን በይበልጥ ተጠቃሚ ያደርገናል ነው ያሉት። ኮምፖስት የአፈርን ይዘት ያሻሽላል፤ ለጠንካራ የእፅዋት ሥርዓት ምቹ ሁኔታ ይፈጥራል፤ የእፅዋት እድገት እና የጤንነት ደረጃን ይጨምራል ብለዋል በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልእክት።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየቤዛ ኩሉ ሃይማኖታዊ ሥርዓት በቅዱስ ላሊበላ በድምቀት እየተከበረ ነው።
Next articleበክልሉ በተፈጠረው የሰላም ችግር በቱሪዝም እንቅስቃሴው ላይ ጉዳት መድረሱን የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አቶ አራጌ ይመር ገልጸዋል፡፡