
ላሊበላ: ታኅሳሥ 29/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በላሊበላ ልዩ መልክ አለው። በተለይም በቀሳውስቱ የሚካሄደው የቤዛ ኩሉ ሃይማኖታዊ ሥርዓት ብዙዎች ሊያዩት የሚጓጉለት አስደናቂ ኹነት ነው።
ይህ የቤዛ ኩሉ ሃይማኖታዊ ሥርዓት በዋዜማው ምሽት ጀምሮ ዋናው ሥርዓት ደግሞ አሁን እየተካሄደ ነው።
ቤዛ ኩሉ በቀሳውስት ዝማሜ፤ በምዕመናን እልልታ እና ጭብጨባ እንዲሁም በተለያዩ ደማቅ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ታጅቦ ነው የሚካሄደው።
ይህንን የቅዱስ ላሊበላ ልዩ መገለጫ ሃይማኖታዊ ሥርዓት በአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዲጂታል ሚዲያ ፌስቡክና ዩቱዩብ ማኅበራዊ ትስስር ገጾች ገጾች በቀጥታ መከታተል ይቻላሉ።
የአሚኮ ሁሉም የማስተላለፊያ ጣቢያዎችም ይህንኑ ሥርዓት ለአድማጭ ተመልካቾች እያደረሱ ነው።
መልካም በዓል!
ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!