
ባሕርዳር: ታኅሳሥ 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የጥር የተጫዋቾች ዝውውር መጀመሩን ተከትሎ ክለቦች የሚፈልጓቸውን ተጫዋቾች ለማግኘት ጥረት እያደረጉ ነው።
ማንቸስተር ዩናይትድ የ22 ዓመቱን ፈረንሳዊ የክሪስታል ፓላስ አማካኝ ማይክል ኦሊሴን የማስፈረም ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለው አስታውቋል፡፡
የ33 ዓመቱ እንግሊዛዊ አማካኝ ጆርዳን ሄንደርሰን ከሳዑዲ አረቢያው አል ኢቲፋክ ወደ እንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ክለቦች ወደ አንዱ መመለስ እንደሚፈልግ ቢቢሲ በድረ ገጹ አስነብቧል::
ዎልቭስ የ31 ዓመቱን የዌስትሃም አጥቂ ዳኒ ኢንግስን ለማስፈረም ድርድር መጀመሩን ቴሌግራፍ በድረ ገጹ ዘግቧል፡፡
ኤቨርተን የ20 ዓመቱን ቱኒዚያዊ አማካኝ ሐኒባል መጅብሪን ከማንቸስተር ዩናይትድ ላይ በውሰት ለማስፈረም ድርድር ላይ ነው።
ዌስትሃም የአያክሱን ኔዘርላንዳዊ የክንፍ መስመር ተጫዋች ስቲቨን በርግዊጅን ለማስፈረም ጫፍ መድረሱን ዘ ሰን አስነብቧል፡፡
የ32 ዓመቱ የማንቸስተር ሲቲው ቤልጄማዊ አማካኝ ኬቨን ደ ብሩይን ወደ ሳዑዲ ፕሮ ሊግ ክለቦች ለመሄድ እየተነጋገረ መኾኑን ዘ ኢንሳደር አስብቧል፡፡
የ26 ዓመቱ አርጀንቲናዊ አጥቂ ላውታሮ ማርቲኔዝ ከኢንተር ሚላን ጋር አዲስ ኮንትራት ሊፈራረም መቃረቡን ፉትቦል ኢታሊያ ዘግቧል፡፡
ባየር ሙኒክ የባርሴሎናውን ተከላካይ ሮናልድ አራውጆን ለማስፈረም የሚያደርጉትን ጥረት አጠናክረው መቀጠላቸውን ስካይ ስፖርት ነው የዘገበው፡፡
የአርሰናሉ አሰልጣኝ አርቴታ የ26 ዓመቱን ስኮትላንዳዊ ተከላካይ ኪይራን ቲየርኒን ከሪያል ሶሴዳድ በውሰት ውል መልሰው ሊያመጡት መኾኑን ቢቢሲ አስነብቧል፡፡
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!