
ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በዱባይ ማራቶን በሁለቱም ጾታዎች ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ውድድሩን በበላይነት አጠናቅቀዋል።
በዚህም በወንዶች ማራቶን
1ኛ አዲሱ ጎበና 2 ሰዓት ከ05 ደቂቃ ከ01 ሰከንድ
2ኛ ለሚ ዱሜቻ 2 ሰዓት ከ05 ደቂቃ ከ20 ሰከንድ እንዲሁም
3ኛ ደጀኔ መገርሳ 2 ሰዓት ከ05 ደቂቃ ከ42 ሰከንድ በመግባት ሲያሸንፉ
በሴቶች ማራቶንም
1ኛ ትዕግስት ከተማ 2 ሰዓት ከ16 ደቂቃ ከ07 ሰከንድ
2ኛ ሩቲ አጋ 2 ሰዓት ከ18 ደቂቃ ከ09 ሰከንድ እንዲሁም
3ኛ ደራ ዲዳ 2 ሰዓት ከ19 ደቂቃ ከ29 ሰከንድ በመግባት አሸናፊ ሆነዋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!