
ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 28/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ሰሜን ጎጃም ዞን የሚገኙት የቋሪት እና የአዴት ወረዳዎች አሥተዳደር እና ነዋሪዎች የልደትን በዓል ምክንያት በማድረግ በቀጣናው ለሚገኘው መከላከያ ሠራዊት የእርድ እንስሳት እና የገንዘብ አበርክተዋል።
የቋሪት ወረዳ አሥተዳደር የእርድ ሰንጋዎችን እና በጎችን አበርክቷል። የአዴት ወረዳ አሥተዳደርም ከሰንጋ እና በጎች በተጨማሪ ለበዓል መዋያ የሚኾን የ38ሺህ ብር አበርክቷል።
የአዴት ከተማ ከንቲባ ንብረት አበጀ እና የቋሪት ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ መዝገቡ ውቤ ስጦታውን አስረክበዋል።
ድጋፉን የተረከቡት ሌተናል ኮሎኔል አለሜ ታደለና ሌተናል ኮሎኔል አርቢሲ መሐመድ ከሕዝብ ወጥተን ለሕዝብ በመቆማችን ግዳጃችንን በስኬት እንደምንፈጽም ሁሉ፣ ኅብረተሰባችንም ያለውን ፍቅርና አክብሮት በእንዲህ አይነት በጎ ነገር መግለጹ ያለንን አንድነት እና ቁርኝት ይበልጥ የሚያጠናክር በመኾኑ ምስጋና እናቀርባለን ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!