
በወልድያ ከተማ አሥተዳደር በሦስቱ ክፍለ ከተሞች ለአረጋውያን እና አቅመ ደካሞች የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል መዋያ ድጋፍ ተደርጓል።
ድጋፍ የተደረገው በከተማው በሚገኙት በእቴጌ ጣይቱ፣ በታላቁ ራስ አሊ እና በየጁ ክፍለ ከተሞች በወጣቶች እና ሴቶች አስተባበሪነት ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች እና ተቋማቶች በተሰበሰበ ሃብት ነው።
የከተማዋ ምክትል ከንቲባ አለምነው ጌጡ እንደገለጹት የማዕድ ማጋራቱ የመደጋገፍ እና የመረዳዳት እሴትን የበለጠ የሚጠናክር መኾኑን ገልጸዋል። ለዚህ በጎ ተግባር መሳካት ትብብር ላደረጉ አካላቶች ሁሉ ምስጋና አቅርበዋል።
ምንጭ፡- የወልደያ ከተማ አሥተዳዳር ኮሙዩኒኬሽን