ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በአዋሬ አካባቢ የተገነባውን የአነስተኛ ወጪ ቤቶች ግንባታ መረቁ።

13

ባሕር ዳር፡ ታኅሣሥ 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እና ቀዳማይት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በአዋሬ አካባቢ በ1 ሺህ 523 ነጥብ 3 ሜትር ካሬ ላይ የተገነባውን ተጨማሪ የአነስተኛ ወጪ ቤቶች ግንባታ መርቀዋል። የተመረቁት ሁለቱ ባለ 11 ወለል ህንፃዎች በሶስት ወራት ጊዜ ተገንብተው የተጠናቀቁ ሲሆኑ በጠቅላይ ሚኒስትሩ የ”መደመር ትውልድ” መጽሓፍ ሽያጭ ገቢ እና ከኦቪድ ኮንስትራክሽን ግሩፕ ድጋፍ የተገነቡ ናቸው።

ሕንጻዎቹ ባለአንድ፣ ባለሁለት እና ባለሦስት የመኝታ ክፍሎች ያላቸው 110 ቤቶች እንዲሁም የታችኛው ወለል ላይ 51 የምድር ቤት ክፍሎችን የያዙ ናቸው። በተጨማሪም የጋራ የእንጀራ እና ዳቦ መጋገሪያ፣ ማብሰያ እና የማጠቢያ አካባቢዎች እንደተካተቱባቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ሁለቱ አፓርትመንቶች በጠባብ ቦታ ላይ ለየአገልግሎቱ በልዩ ሁኔታ የመጠቀም ጥበብ ያረፈባቸው ሲሆኑ፤ ሁሉም ቤቶች ሙሉ እቃ የተሟላላቸው መሆኑ ተገልጿል። ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በዚሁ ወቅት÷ ባለሃብቶች በበጎ አድራጎት እና ፈጠራ የኦቪድ ኮንስትራክሽን ግሩፕ አርዓያነትን እንዲከተሉ ጥሪ አቅርበዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስ ፀጉርና ከመቅደላ የተወሰዱ ታሪካዊ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ።
Next articleልደትን በላሊበላ ለማክበር የሚገቡ እንግዶችን እየተቀበሉ ማስተናገድ መጀመራቸውን የላሊበላ ነዋሪዎች ገለጹ።