የልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስ ፀጉርና ከመቅደላ የተወሰዱ ታሪካዊ ቅርሶች ወደ ኢትዮጵያ ተመለሱ።

24

ባሕርዳር: ታኅሳሥ 27/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የልዑል አለማየሁ ቴዎድሮስ ፀጉር እና በመቅደላ ጦርነት ወቅት በእንግሊዝ ጦር የተወሰዱ ታሪካዊ ቅርሶች ተመለሱ። የተመለሱት ታሪካዊ ቅርሶች ሁለት በብር የተለበጡ ዋንጫዎች፣ አንድ የቀንድ ዋንጫ፣ ደብዳቤዎች እንዲሁም አንድ ጋሻ ከእንግሊዝ ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል።

በእንግሊዝ የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ ቅርሶቹን ይዘው እንደተመለሱ ተገልጿል።
ለቅርሶቹ የኢትዮጵያ ቅርስ ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አበባው አያሌው(ረ/ፕ) አቀባባል እንዳደረጉም ተገልጿል፡፡
ቅርሶቹን ማስመለስ መቻሉ ለኢትዮጵያ የዲፕሎማሲ ድል መሆኑንም አምባሳደር ተፈሪ ተናግረዋል።


በእንግሊዝ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቅርስ አስመላሽ ኮሚቴና ሼኸራዛድ ፋውንዴሽን ጋር በመተባበር ባለፈው መስከረም ቅርሶቹን ማስመለሳቸው ይታወሳል።

መንግሥት ከኢትዮጵያ ተዘርፈው በተለያዩ ሀገራት ሙዚየም የሚገኙ ቅርሶችን ለማስመለስ የሚያደርገውን ዲፕሎማሲያዊ ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የተደረገው የሰላም ጥሪ ሕዝብ እና መንግሥትን ያግባባ ነው” አቶ ደሳለኝ ጣሰው
Next articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በአዋሬ አካባቢ የተገነባውን የአነስተኛ ወጪ ቤቶች ግንባታ መረቁ።