“ዘንድሮ ከ2 ቢልየን በላይ ቡና፣ ከግማሽ ቢልየን በላይ ፍራፍሬ እና ከ400 ሚልየን በላይ የሻይ ተክል ዝግጅት ተጀምሯል” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)

13

ባሕርዳር: ታኅሳሥ 26/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) እንዳሉት ዘንድሮ ከ2 ቢልየን በላይ ቡና፣ ከግማሽ ቢልየን በላይ ፍራፍሬ እና ከ400 ሚልየን በላይ የሻይ ተክል ዝግጅት ተጀምሯል።

እስካሁን ከነበረን በከፍተኛ ሁኔታ ተሻሽሎ በቡና፣ በፍራፍሬ እና በሻይ ላይ ያተኮር ዝግጅት እያደረግን ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ።

ይሄንን በደንብ ተክለን ወደ ምርት ካሳደግነው፣ በአጠቃላይ ኢኮኖሚያችን እና በአየር ንብረት ጥበቃ ላይ የሚኖረው ሚና ከፍተኛ ይሆናል ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleልደትን በላሊበላ ለማክበር የሚገቡ እንግዶችን እየተቀበሉ ማስተናገድ መጀመራቸውን የላሊበላ ነዋሪዎች ገለጹ።
Next article“በመንግሥት እና በግሉ ዘርፍ ሊሸፈኑ ያልቻሉ ችግሮችን በመሸፈን በተቋቋምንበት ዓላማ ልክ በስፋት እንሠራለን” የኢትዮጵያ የኅብረት ሥራ ኮሚሽን