
አዲስ አበባ: ታኅሳሥ 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የአብሮነት ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ በየዓመቱ ኀዳር ስድስት ቀን “የመቻቻል” ቀን ተብሎ እንዲከበር በዩኔስኮ መወሰኑ ይታወሳል፡፡
ይህ ቀን ታዲያ በኢትዮጵያም የአብሮነት ሳምንት ተብሎ ከታኅሣሥ 20 ቀን ጀምሮ “ብዝኃነትን መኖር” በሚል መሪ መልዕክት በተለያዩ ሁነቶች ስታከብረው ቆይታለች።
ዛሬም ለ14ኛ ጊዜ እየተከበረ በሚገኘው የአብሮነት ቀንም ሚኒስትሮች፣ የክልል እና የከተማ አሥተዳደር ተወካዮች፣ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና አምባሳደሮችን ጨምሮ 100 ሺህ የዩኒቨርሲቲ የማኅበረሰብ ክፍሎች በደቦ ፕላትፎርም በቀጥታ እየተሳተፉ ነው ተብሏል።
የባሕል እና ስፖርት ሚኒስቴር ከሌሎች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቶች ጋር በጋራ ባዘጋጁት በዚህ መድረክ አብሮነት ላይ ትኩረታቸውን ያደረጉ ጥናታዊ ጹሑፎች ቀርበው ውይይቶች ይደረጋሉም ተብሎ ይጠበቃል።
ዘጋቢ፡- ቤተልሄም ሰለሞን
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!