
ደሴ: ታኅሳሥ 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ፋውንዴሽኑ በደሴ ከተማ የልደት በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ60 አባዎራዎች እና እማዎራች 75 ሺህ ብር ወጭ በማድረግ ማእድ በማጋራት ድጋፉ አድርጓል፡፡
ድጋፍ የተደረገላቸው አባዎራዎች እና እማዎራዎች የከፋ ችግር ያለባቸው እና ከ5 እድሮች የተውጣጡ መኾናቸው ተገልጿል፡፡ ድጋፉ የዶሮ፣ የእንቁላል፣ የዘይት እና የገንዘብ ሲሆን በተደረገላቸው ድጋፍም መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡
በ2012 ዓ.ም የተቋቋመው ፋውንዴሽኑ ከዚህ በፊት በትምህርት ቤቶች የጽሕፈት መሳሪያ ችግር ላለባቸው ተማሪዎች፣ የጤና መድን መክፈል ለማይችሉ ከ10 በላይ ሰዎች እንዲኹም ሌሎች የአልባሳት እና የምግብ ሸቀጦች ድጋፍ ማደረጉ ይታወሳል፡፡
ዘጋቢ፡ መሐመድ በቀለ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!