ለልደት እና ጥምቀት በዓላት በአማራ ክልል ከ3 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሊትር በላይ ዘይት እንደሚሰራጭ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ገለጸ።

49

ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ለኢየሱስ ክርስቶስ ልደት በዓል እና ለጥምቀት በአማራ ክልል የሚሰራጨውን ከ3 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሊትር በላይ ዘይት ሥራ የሚያከናውነው የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን መኾኑን የንግድ እና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፍስሃ ይታገሱ ገልጸዋል።

የጸጥታ ችግሮች ባሉባቸው የክልሉ ቦታዎች የንግድ ሥራዎች ኮርፖሬሽን ከፀጥታ ኀይሎች ጋር በመኾን የዘይት አቅርቦቱን ወደ ኅብረተሰቡ እንደሚያቀርቡ ሚኒስትር ዴኤታው ተናግረዋል።

በመንግሥት የሚቀርበው የዘይት ምርት በክልሎች እና ከተማ አሥተዳደሮች ያልተሰራጨ 9 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሊትር ዘይት የመንግሥት የልማት ድርጅቶች እና የዘይት ፋብሪካዎች ወስደው እንዲያሰራጩት ተደርጓልም ተብሏል።

መንግሥት የአቅርቦት ችግር እንዳይከሰት ከተለያዩ አቅራቢዎች ጋር እየሠራ መኾኑን የገለጹት ደግሞ በሚኒስቴር መሥራቤቱ የሀገር ውስጥ ንግድ እና ሸማቾች ጥበቃ ተቆጣጣሪ መስከረም ባህሩ ናቸው።

ሚኒስቴር መሥራቤቱ ሕዝቡ ተረጋግቶ በዓሉን እንዲያሳልፍ አሳስበው የዋጋ ጭማሪ ሲኖር ወደ መንግሥት ማመልከት እንደሚችልም ነው ያስገነዘቡት።

ዘጋቢ፡- እዮብ ርስቴ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበኢትዮጵያ ፕሪሜየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስን ከመቻል የሚያገናኘው ጨዋታ ይጠበቃል።
Next articleበሕገ ወጥ መንገድ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎች ወደ ሕጋዊ መስመር እንዲገቡ የኢሜግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ጥሪ አቀረበ፡፡