
ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ማንቸስተር ዩናይትድ የአሮን ዋን-ቢሳካን ኮንትራት በ12 ወራት አራዝሟል ሲል ሜይል ዘግቧል፡፡
የ31 ዓመቱ ግብጻዊ አጥቂ ሞሃመድ ሳላህ ወደ ሳውዲ ፕሮ ሊግ ለመሄድ ከፍተኛ ፍላጎት አሳይቷል፤ ነገር ግን እናት ክለቡ ሊቨርፑል የተጫዋቹን ውል ለማራዘም መቃረቡን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
ቦሩሲያ ዶርትሙንድ የ21 ዓመቱን ሆላንዳዊ የቼልሲ የግራ መስመር ተከላካይ ኢያን ማሴን ለማስፈረም ተስፋ አድርገዋል ሲል ቴሌግራፍ አስነብቧል፡፡
ማንቸስተር ዩናይትድ የክሪስታል ፓላሱን የክንፍ መስመር ተጫዋች የ22 ዓመቱን ማይክል ኦሊሴን በሰር ጂም ራትክሊፍ ዘመን በኦልድትራፎርድ የመጀመሪያ ፈራሚ ለማድረግ ፍላጎት አሳይቷል ተብሏል፡፡
ክሪስታል ፓላስ እንግሊዛዊውን አጥቂ ኤዲ ንከቲያን ለማስፈረም ፍላጎት አሳይቷል፡፡ ነገርግን አርሰናል ተስማሚ ተተኪ ካላገኙ በስተቀር የ24 ዓመቱን ተጫዋች እንደማይሸጥ አስታውቋል፡፡
በፈረንሳዩ ሊግ 1 የሚሳተፈው ሊዮን የዌስትሃምን እና አልጄሪያዊውን የክንፍ መስመር ተጫዋች ሰይድ ቤንራህማን ማስፈረም ፈልገዋል። ዎልቭስ እና ፉልሀምም የ28 ዓመቱን ተጫዋች ለማስፈረም ንግግር መጀመራቸወን ሚረር ዘግቧል፡፡
የ27 ዓመቱ ጀርመናዊው አጥቂ ቲሞ ወርነር የማንቸስተር ዩናይትድ ከፍተኛ የዝውውር ኢላማ ሆኖ ብቅ ብሏል። ሞናኮ ለ27 ዓመቱን ጀርመናዊ ተከላካይ ቲሎ ኬሬር በውሰጥ ዝውውር ለመውሰድ ከዌስትሀም ጋር እየተነጋገረ ነው ተብሏል።
ሼፊልድ ዩናይትድ የ24 ዓመቱን የቪላሪያል የፊት መስመር አጥቂ ቤን ብሬቶን ዲያዝ በውሰት ለማስፈረም ተቃርቧል። ዎልቭስ የ18 ዓመቱን ጋቦናዊ አማካኝ ኖሃ ሌሚናን ከፓሪስ ሴንት ዠርሜይን በውሰት ለማስፈረም ድርድር ጀምሯል፡፡
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!