“የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ሲከበር የተቸገሩትን ሁሉ በመልካም ተግባር በማሰብ ይሁን” የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን

55

አዲስ አበባ: ታኅሳሥ 25/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን የገና በዓልን በማስመልከት የመልካም ምኞት መግለጫ አስተላልፋለች። መግለጫውን የሰጡት ሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ አምላክ ከሰው ልጆች ጋር ያለውን ግንኙነት ለማደስ ሰማይን እና ምድርን ለማስታረቅ እንደ ሰው ስጋን ለብሷል ብለዋል።

የኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል ሲከበርም ከራስ ወዳድነት በወጣ፣ የተራቡ የታረዙና የተጠሙ በሚታሰቡበት፣ የተበደሉ የታመሙና የተፈናቀሉ የሚታወሱበት እንዲሁም በተለያዩ ምክንያቶች ችግር ውስጥ ለገቡ ወገኖች አለኝታ የምንኾንበት ኾኖ መከበር ይገባዋል ብለዋል።

ከዚህ ባሻገር “ለተፈጠሩ ችግሮች ሁሉ እግዚአብሔር መፍትሄ ይሰጠን ዘንድ በፀሎት እንትጋ” ብለዋል ብፁዕ ካርዲናል አቡነ ብርሃነኢየሱስ በመልዕከታቸው።

ዘጋቢ፡- እንዳልካቸው አባቡ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሰሊጥ ምርት ግብይትን ከሕጋዊ ሥርዓቱ ውጪ አላስፈላጊ ጥቅም ለማግኘት በሚሠሩ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የአማራ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ ገለጸ።
Next articleሕዝቡ በፍትሕ ሥርዓቱ ላይ እምነት እንዲኖረው እንዲሠራ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤ ታገሰ ጫፎ አሳሰቡ፡፡