መገናኛ ብዙኀን ችግሮች እንዲፈቱ እየሠሩት ያለው ሥራ የሚመሰገን እንደኾነ ተቋማት ገለጹ፡፡

22

አዲስ አበባ: ታኅሳሥ 24/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ ሥራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢፌዴሪ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ጋር በመተባበር ለመገናኛ ብዙኀን የሥራ ኀላፊዎች የግንዛቤ ማሰጨበጫ እና የውይይት መድረክ አካሂዷል።

የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ደሲሳ “እየሠራናቸው ያሉትን ሥራዎች ሚዲያው እንዲገነዘብ እና በቀጣይ ለምንሠራቸው ሥራዎች ለሚዲያ ባለሙያዎች ግንዛቤ ለመፍጠር የተዘጋጀ መድረክ ነው” ብለዋል፡፡

በተለያዩ ጊዜያት የሚሠሩ ሥራዎችን እየተከታተሉ ለሕዝብ የሚያደርሱት መገናኛ ብዙኀን በመኾናቸው ለዘርፉ ባለሙያዎች ቅድሚያ ሰጥቶ ውይይት ማድረግ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡ መገናኛ ብዙኀኑ እየሠሩ ላሉት ሥራ እና ችግሮች እንዲፈቱ ለሚሰጡት ሀሳብ እና አስተያየትም ምሥጋናቸውን አቅርበዋል።

የሥራ እና ክህሎት ሚኒስቴር ሚኒስትር ሙፈሪያት ካሚል መገናኛ ብዙኀን ብሔራዊ መግባባትን የመፍጠር ኀላፊነታቸውን በሚገባ መወጣት መቻል አለባቸው ብለዋል፡፡ መገናኛ ብዙኀን በተቋማቸው ውስጥ ያሉ ጉዞዎችን ዕለት ከዕለት እየተከታተሉ በዜና እና በፕሮግራም በማስተዋወቅ እና በማስገንዘብ ኀላፊነታቸውን በመወጣታቸው ምሥጋና ይገባቸዋልም ብለዋል።

“ይህን መድረክ ማዘጋጀት ያስፈለገውም መረጃዎችን ለሕዝብ ለማድረስ ከመገናኛ ብዙኀን የሚቀርብ ባለመኖሩ እና በጋራ መሥራት ስለሚጠይቅ ነው“ ሲሉ ተናግረዋል።

ዘጋቢ፡- ቤቴል መኮንን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleቶትንሃም ፓፔ ማታር ሳረር ለስድስት ዓመት ተኩል በክለቡ እንዲቆይ አዲስ የኮንትራት ውል አስፈረመ።
Next articleከ1 ቢሊዮን ብር በጅቶ የመሰረተ ልማት ግንባታ እያካሄደ መኾኑን የኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳደር ጉጸ።