ወልዲያ በሚካሄደው ክልል አቀፍ የስፖርት ውድድር ላይ ዋንጫ ለማንሳት የሚያስችል ዝግጅት ማድረጉን የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳድር አስታወቀ፡፡

330

ዘመናዊ የስፖርት ውድድሩ ከየካቲት 24/2012 እስከ መጋቢት 6/2012 ዓ.ም በወልዲያ ከተማ ይካሄዳል፡፡

የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ከየካቲት 7 እስከ 15/2012 ዓ.ም ዘመናዊ የስፖርት ውድድሮችን ሲያካሂድ ቆይቷል፡፡ በብሔረሰብ አስተዳደር ደረጃ ከሚሴ ከተማ አስተናጋጅነት ሲካሄድ በቆየው ውድድር ከአማራ ከልል 5 ወረዳዎች እና ከ2 የከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ ከ650 በላይ ስፖርተኞች ተሳትፈውበታል፡፡ ቴኳንዶ፣ እግር እና መረብ ኳስ፣ ጠረጴዛ ቴኒስን ጨምሮ በ11 የስፖርት አይነቶች ውድድር መካሄዱን የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር የስፖርት ተጠሪ ጽህፈት ቤት የስፖርት ቡድን መሪ አቶ ፀጋዬ በቀለ ተናግረዋል፡፡

ውድድሩ የብሔረሰብ አስተዳደሩን የስፖርት አቅሙን ለመፈተሽ እንዳስቻለውም ነው የተናገሩት፡፡ ከየካቲት 24/2012 እስከ መጋቢት 6/2012 ዓ.ም በወልዲያ ከተማ በሚካሄደው ክልል አቀፍ ውድድር ላይ ዋንጫን ለማንሳት የሚያስችል ዝግጅት ማድረጋቸውንም አቶ ፀጋዬ አስታውቀዋል፡፡

በሁሉም ውድድሮች ብቁ ዳኛ አለመኖሩ ችግር እንደነበረም አቶ ፀጋዬ ተናግረዋል፡፡

ወደፊት በቂ ስልጠና በመሥጠት ችግሩን ለመቅረፍ እንደሚሠሩም ነው የተናገሩት፡፡ ትናንት በተጠናቀቀው ውድድር ከሚሴ ከተማ የአጠቃላይ አሸናፊ ሆኗል፡፡

ዘጋቢ፡- ይማም ኢብራሂም ከከሚሴ

Previous article“የክልሉ ሕዝብ የተጋረጡበትን ዘርፈ ብዙ ችግሮችን ለመቅረፍ ሳንቲም ሳትቀር መቆጠብ አለበት፡፡” አቶ መኮንን የለውምወሰን
Next articleበተለያዩ ምክንያቶች በእሥር ላይ የሚገኙ ግለሰቦች ክስ እንዲቋረጥ መንግሥት ወሰነ።