ዛሬ ሀገር አቀፍ የሕግ አውጪዎች መድረክ በሐረር ከተማ ይካሄዳል።

35

ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 24/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ሀገር አቀፉ የሕግ አውጪዎች መድረክ የፌዴራል፣ የክልል እና የሁለቱ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባዔዎች እና ሌሎችም በተገኙበት ዛሬ በሐረር ከተማ ይካሄዳል።

መድረኩ በዓመት ሁለት ጊዜ የሚካሄድ መኾኑ ተገልጿል። በመድረኩ የፌዴራል፣ የክልል እና የከተማ አሥተዳደር ምክር ቤቶች በጋራ ጉዳዮቻቸው ዙሪያ የሚመክሩበት ነው።

የልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበት መሆኑንም ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ዛሬ በሐረር ከተማ የሚጀምረው ሀገር አቀፍ የሕግ አውጪዎች የጋራ መድረክ ለ4ኛ ጊዜ የሚካሄድ ሲኾን 3ኛው ዙር በሱማሌ ክልል በጅግጅጋ ከተማ መካሄዱን ይታወሳል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎች ድሬዳዋ ገቡ።
Next articleየለማውን ጥጥ ለኢንዱስትሪዎች ግብዓት በሚውል መልኩ በጥራት እየተሰበሰበ መኾኑን የምዕራብ ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ ገለጸ።