የሕዝብ ተወካዮች እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤዎች ድሬዳዋ ገቡ።

25

ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ነገ ለሚጀመረው ሀገር አቀፍ የሕግ አውጪዎች የጋራ መድረክ ለመታደም የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ታገሰ ጫፎ እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ አገኘሁ ተሻገር ድሬዳዋ ከተማ ገብተዋል።

ሀገር አቀፍ የሕግ አውጪዎች መድረክ ነገ በሐረር ከተማ መካሄድ ይጀመራል። ከሁለቱ ምክር ቤቶች አፈ-ጉባኤዎች በተጨማሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛ መሪዎች፣ የክልል ምክር ቤቶች አፈ ጉባኤዎች እና ከፍተኛ መሪዎች ድሬዳዋ ከገቡት መካከል ናቸው።

ኢዜአ እንደዘገበው ተሳታፊዎች ድሬዳዋ ከተማ ሲገቡ የሐረሪ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ሱልጣን አብዱሰላም፣ የሐረሪ ጉባዔ አፈ ጉባዔ መህየዲን አህመድ፣የድሬዳዋ ምክር ቤት አፈ ጉባዔ ፈቲያ አደን እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ድሬዳዋ ዓለምአቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በአዲስ መልክ የሸማች ማኅበራትን በማቋቋም ዘመናዊ እና ሕጋዊ የንግድ ሥርዓትን በመገንባት የኑሮ ውድነቱን ለማቃለል እንሠራለን” ዶክተር አሕመዲን ሙሐመድ
Next articleዛሬ ሀገር አቀፍ የሕግ አውጪዎች መድረክ በሐረር ከተማ ይካሄዳል።