
ባሕርዳር: ታኅሳሥ 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የ38 ዓመቱ ዋይኒ ሩኒ በእንግሊዝ ሻምፒዮንስ ሺፕ በመሳተፍ ላይ የሚገኘው የበርሚንግሃም ሲቲ ቡድን አሠልጣኝ ነበር፡፡
ሩኒ እኤአ ጥቅምት 11 ቀን 2023 ቡድኑን ማሰልጠን ከጀመረ ጀምሮ 15 ጨዋታዎችን በማድረግ በዘጠኙ ተሸንፏል፡፡
በመኾኑም የቡድኑ አሥተዳደር ባደረገው ስብሰባ አሠልጣኙ ውጤታማ ሥራ ባለማከናወኑ ለማሰናበት መገደዱን ሜይልኦን ላይን ዘግቧል፡፡
በርሚንግሃም ሲቲ በሻምፒዮን ሺፑ 26 ጨዋታዎችን አድርጎ በ12 ጨዋታዎች ተሸንፎ ፣ በሰባቱ አቻ እንዲሁም በሰባቱ በማሸነፍ በ28 ነጥብ 20ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡
የቀድሞ የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድንና የማንቸስተር ዩናይትድ አምበል ዋይኒ ሩኒ ቀደም ሲል ደርቢ ካውንቲ እና ዲሲ ዩናይትድን በአሠልጣኝነት መምራቱን ቢቢሲ ስፖርት በዘገባው አስታዉሷል፡፡
በሙሉጌታ ሙጨ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!