
ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በምዕራብ ጎንደር ዞን “ሰላማችን ለነጭ ወርቅ ምድራችን” በሚል መሪ ቃል ነክልል እና ዞን አመራሮች፣ ከፍተኛ የጸጥታ የሥራ ኀላፊዎች እና የሀገር ሽማግሌዎች ውይይት እና ምክክር እያካሄዱ ነው።
በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ጉዳዮች አስተባባሪና የሰላምና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ ደሳለኝ ጣሰው “ሰላም የሁሉም ነገር መነሻ ነው” ሲሉ ተናግረዋል። በመኾኑም ለሰላም ትልቅ ትርጉም ሰጥተን በመሥራት የሕዝብን ደኅንነት ጠብቆ ለማስቀጠል የምክክር መድረኮች ፋይዳቸው ጉልህ በመኾኑ አስገንዝበዋል። ውይይቶች መፍትሔ ላይ ያተኮሩ መኾን አለባቸው ሲሉም አንስተዋል።
የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ቢክስ ወርቄ በሕዝብ፣ በመንግሥት እና በጸጥታ አካላት ትብብር የዞኑ ሰላም እየተጠበቀ ነው ብለዋል። ይህ የቅንጅት ጥረት ውጤት ያስመዘገበ ስመኾኑም ተናግረዋል። የዞኑን ሰላም በማስቀጠል የሚታዩ ችግሮችን ደግሞ መፍትሔ ለመስጠት እየተሠራ ነው ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!