ዌስትሃም የቶማስ ሱሴክን ውል አራዘመ

13

ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 23/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የዌስት ሃም አማካይ ቶማስ ሱሴክ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር እስከ ሰኔ 2027 የሚያቆየውን አዲስ ውል ፈርሟል። ተጫዋቹ በዚህ የውድድር ዘመን ለክለቡ ስምንት ጎሎችን አስቆጥሯል።

የ28 ዓመቱ የቼክ ሪፐብሊክ ዜጋ ለዌስት ሃም በ182 ጨዋታዎች ተሰልፎ 30 ግቦችን አስቆጥሯል ፡፡

የተጫዋቹ የኮንትራት ውል የሚጠናቀቀው በቀጣዩ የክረምት ወራት ነበር፡፡ ይሁንና ክለቡ ውሉን እስከ ሰኔ 2027 አራዝሞታል፡፡

ሱሴክ የውሉን መራዘም አስመልክቶ “አሁን ውል በማደሴ ዌስትሃም ቤቴ እንደኾነ ይሰማኛል፡፡ ስለኾነም በዚህ ታላቅ ክለብ ወደፊት የበለጠ በመሥራት ፍላጎቴን ማሳካት እፈልጋለሁ” ብሏል።

አሰልጣኝ ዴቪድ ሞይስ በበኩላቸው “ሱሴክ ለዌስት ሃም ድንቅ ብቃቱን እያሳየ ይገኛል፤ ክለቡ ላስመዘገበው እድገት እና ላስመዘገብነው ስኬት ትልቅ ሚና ተጫውቷል” ሲል ተናግሯል።

ዌስት ሃም በፕሪሜየር ሊጉ 19 ጨዋታዎችን አድርጎ በ10ሩን አሸንፏል፡፡ በሶስት ጨዋታዎች አቻ ወጥቶ እና በስደስት ተሸንፎ በ33 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዞ ይገኛል።

በሙሉጌታ ሙጨ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ከሶማሌ ላንድ ጋር የተደረገው ስምምነት ለዘመናት ኢትዮጵያ ላይ የተቆለፈውን በር የከፈተ ነው” የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት
Next articleኢትዮጵያ ከሶማሌ ላንድ ጋር ያደረገችዉ የወደብ ስምምነት እንዳስደሰታቸው የደሴ ከተማ ነዋሪዎች ገለጹ፡፡