“ከሶማሌ ላንድ ጋር የተደረገው ስምምነት ለዘመናት ኢትዮጵያ ላይ የተቆለፈውን በር የከፈተ ነው” የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት

39

ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ኢትዮጵያና ሶማሌ ላንድ በትናንትናው እለት በወደብ ልማትና የጋራ ተጠቃሚነት ላይ የሁለትዮሽ ስምምነት ተፈራርመዋል።

ጉዳዩን በማስመልከት ለመገናኛ ብዙኃን መግለጫ የሰጠው የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎትም ይህ ስምምነት እንደ ሀገር ትልቅ ድል የተመዘገበበት ነው ብሏል።

መግለጫውን የሰጡት የባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ አገልግሎት ዋና ሥራ አስፈጻሚ በሪሶ አመሎ (ዶ.ር) “ከሶማሌ ላንድ ጋር የተደረገው ስምምነት ለዘመናት ኢትዮጵያ ላይ የተቆለፈውን በር የከፈተ ነው” ብለዋል።

ይህ ስምምነት የትራንስፖርት እና የንግድ ወጪን የሚቀንስ ሉዓላዊነትን ለማስጠበቅ የሚያግዝ እና ኢኮኖሚን የሚያጠናከር በመኾኑ ሚናው የጎላ መኾኑንም ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል።

ይህ ስምምነትም የባሕር ትራንስፖርት እና ሎጅስቲክስ አገልግሎት አሁን ካለው አሠራር በላይ ራሱን እንዲያጎለብት እና እንዲያዘምን ትልቅ የቤት ሥራ የሰጠ በመኾኑ በስፋት ይሠራል ብለዋል።

ዘጋቢ፡- እንዳልካቸው አባቡ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና የሶማሌላንድ ፕሬዚደንት ሙሴ ቢሂ አብዲ ታሪካዊ የኾነ የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።
Next articleዌስትሃም የቶማስ ሱሴክን ውል አራዘመ