
ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 22/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ የብሪክስ አባል ለመኾን ያቀረበችው ጥያቄ ተቀባይነት ካገኘ ወራት አልፈዋል። ሀገሪቱ በዛሬው ዕለት ብሪክስን በይፋ ተቀላቅላለች።
ኢትዮጵያን ጨምሮ አምስት ሀገራት ናቸው በዛሬው ዕለት ብሪክስን በይፋ የተቀላቀሉት። ከኢትዮጽያ በተጨማሪ ሳዑዲ አረቢያ፣ ግብጽ፣ የተባበሩት አረብ ኤሚሬቶች እና ኢራን በዛሬው ዕለት ብሪክስን በይፋ ስለመቀላቀላቸው የዘገበው ሲጂቲኤን ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!