
ጎንደር: ታኅሳሥ 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ከተማ አሥተዳደር በአዘዞ ጠዳ ክፍለ ከተማ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ የሚመሩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የመኖሪያ ቤት ተጠቃሚ ለማድረግ የመሰረት ድንጋይ ተቀምጧል።
የአዘዞ ጠዳ ክፍለ ከተማ የከተማ እና መሰረተ ልማት ዘርፍ ዋና ሥራ አሥኪያጅ ሀብቴ ማሞ በክፍለ ከተማው ከ2 ሺህ በላይ በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ውስጥ የሚገኙ ነዎሪዎች የመኖሪያ ቤት ጥያቄ እንዳላቸው ጠቅሰዋል።
በበጀት ዓመቱ 250 ነዋሪዎችን የቤት ባለቤት ለማድረግ መታቀዱን ተናግረዋል።
የአዘዞ ጠዳ ክፍለ ከተማ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ይሁን ዳምጤ ከማኅበረሰቡ የመልካም አሥተዳደር ጥያቄዎች ውስጥ የመኖሪያ ቤት ችግር ተጠቃሽ መኾኑን አመላክተው ችግሩን ለመፍታት ክፍለ ከተማው እየሠራ መኾኑን ጠቁመዋል።
የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ቤቶች ልማት ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሰላማዊት ቦጋለ በጎንደር ከተማ የመኖሪያ ቤት ጥያቄ ያላቸው ከ10 ሺህ በላይ ነዋሪዎች መኖራቸውን የተናገሩ ሲኾን በበጀት ዓመቱ ከ2 ሺህ በላይ የሚኾኑ ነዎሪዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ መታቀዱን አስታውቀዋል።
በዝቅተኛ የሩሮ ደረጃ የሚገኙ ነዋሪዎችን የቤት ችግር ለመፍታት የማኅበረሰቡ ተሳትፎ አስፈላጊ መኾኑ ተመላክቷል።
ዘጋቢ:- ቃልኪዳን ኃይሌ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!