
ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን በሰሜን ወሎ ዞን ሀራ ከተማ አሥተዳደር በማኅበረሰቡ ትብብር እየተገነባ የሚገኝ ባለሦስት ፎቅ የቢሮ ግንባታ ጎብኝተዋል።
የቢሮ ግንባታው ለከተማ አሥተዳደሩ የቢሮ እጥረትን የሚያቃልል፤ ደረጃውንም የሚያሻሽል እንደኾነ ተገልጿል። ሙሉ በሙሉ በማኅበረሰቡ መዋጮ ነው እየተገነባ የሚገኘው።
ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን የሀራ ከተማ ሕዝብ በትብብር እያስገነባ የሚገኘው ለቢሮ አገልግሎት የሚውል ሕንፃ ተሞክሮ የሚቀመርበት ነው ብለዋል።
የከተማዋ ነዋሪዎች ሰላምን በማስጠበቅና በልማት ሥራዎች ተሳትፏቸው የሚመሠገን እንደኾነ የገለጹት ምክትል ርእሰ መሥተዳድሩ የዞን እና የክልል ድጋፍ እንደማይለያቸም አረጋግጠዋል።
የሀራ ከተማ ነዋሪዎች እስካሁን ከ20 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ አድርገዋል ።
ዘጋቢ:- ከድር አሊ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!