
ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ምክር ቤት ባካሄደው 1ኛ አስቸኳይ ጉባኤ አቶ ቴዎድሮስ እንዳለውን የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ዋና አሥተዳዳሪ አድርጎ ሹሟል።
ምክር ቤቱ ለአስፈጻሚ ተቋማት በዋና አሥተዳዳሪው የቀረቡ እጩ ተሿሚዎችን ሹመት መርምሮም አጽድቋል።
በዚህም መሠረት:-
1ኛ. አቶ አይተነው ታዴን የብሔረሰብ አሥተዳደሩ ምክትል አሥተዳዳሪ እና የከተማ እና መሠረተ ልማት መምሪያ ኀላፊ
2ኛ. አቶ ደስታው ዓለሙን የትምህርት መምሪያ ኀላፊ
3ኛ. ወይዘሮ ትዕግስት መኩሪያን የሲቪል ሰርቪስ እና የሰው ሀብት መምሪያ ኀላፊ
4ኛ. አቶ ትዕዛዙ አበበን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ኀላፊ
5ኛ. አቶ እውነቱ አወቀን የውኃ ሀብት ልማት መምሪያ ኀላፊ
6ኛ. አቶ ያረጋል ያየህን የንግድ እና ገበያ ልማት መምሪያ ኀላፊ
7ኛ. አቶ ጥላሁን እሸቴን የመንገድ መምሪያ ኀላፊ በማድረግ ሾሟል።
ተሿሚዎቹ ኅብረተሰቡን በማሳተፍ የብሔረሰብ አሥተዳደሩን ሕዝብ የልማት እና የመልካም አሥተዳደር ጥያቄዎች ለመመለስ ተግተው እንደሚሠሩ ተናግረዋል።
ዘጋቢ፦ ሳሙኤል አማረ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!