መንግሥት ከ9 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ድጎማ ማድረጉን የትራንስፖርትእና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ።

20

ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ)መንግሥት በ2016 በጀት ዓመት አምስት ወራት ለሕዝብ አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ከ9 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ድጎማ ማድረጉን ትራንስፖርትእና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ባለፉት አምስት ወራት 5 ሺህ 786 ተሸከርካሪዎች ከነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚነት መታገዳቸውንም ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ አመላክቷል፡፡

በትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ሚኒስቴር ብሔራዊ የታለመለት ነዳጅ ድጎማ ፕሮጀክት አስተባባሪ አቶ ሰልማን መሐመድ እንደገለጹት የታለመለት የነዳጅ ድጎማው ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የማኅበረሰብ ክፍሎች የኑሮ ጫና ለማቃለል ዓላማ ያለው ነው ብለዋል፡፡

መንግሥት የነዳጅ ድጎማን ከሐምሌ 2014 ዓ.ም ጀምሮ ተግባራዊ እያደረገ ይገኛል። በዚህም በ2016 በጀት ዓመት አምስት ወራት ለሕዝብ አገልግሎት ሰጪ ተሽከርካሪዎች ከ9 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ድጓማ አድርጓል ተብሏል፡፡

ኢፕድ እንደዘገበው የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ተሽከርካሪዎችን በመለየት የነዳጅ ድጎማ ተጠቃሚ እንዲኾኑ እየተደረገ ነው ያሉት ፕሮጀክት አስተባባሪው በ2016 በጀት ዓመት አምስት ወራት ብቻ ለታለመለት የነዳጅ ድጎማ ከ9 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በላይ ወጭ ተደርጓል ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article30ኛዉ የአማራ ክልል ሀገር አቋራጭ የአትሌቲክስ ውድድር በደብረ ብርሃን ከተማ እየተካሄደ ነው።
Next articleየአዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን ሰጠ።