30ኛዉ የአማራ ክልል ሀገር አቋራጭ የአትሌቲክስ ውድድር በደብረ ብርሃን ከተማ እየተካሄደ ነው።

21

ደብረ ብርሃን: ታኅሳሥ 21/2016 ዓ.ም (አሚኮ) 30ኛው የአማራ ክልል ሀገር አቋራጭ የአትሌቲክስ ውድድር የሚካሄደዉ በሁለቱም ጾታ በስድስት፣ በስምንት እና በ10 ኪሎ ሜትር ርቀት ነው።

በውድድሩ በክልሉ የሚገኙ ዞኖች እና ክለቦች እየተሳተፉ ይገኛሉ።

ውድድሩን ያስጀመሩት የአማራ ክልል የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል ጥላሁን አማረ ናቸው።

የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባሉ ውድድሩ ጥር/2016 ዓ.ም ለሚካሄደዉ ለ41ኛው የጃንሜዳ ሀገር አቋራጭ ውድድር የአማራ ክልልን የሚወክሉ አትሌቶችን ለመምረጥ እንደኾነ አብራርተዋል።

አቶ ጥላሁን የተቀዛቀዘውን የአትሌቲክስ ስፖርት ለማነቃቃት ታስቦ የተካሄደ ውድድር ስለመኾኑም ነው ያስገነዘቡት።

ወቅታዊ አቋማቸውን ለመፈተሽ ውድድሩ የሚያግዝ በመኾኑ መደሰታቸውን በውድድሩ የተካፈሉ አትሌቶች ተናግረዋል።

በሁሉም ውድድሮች የተሻለ ሰዓት ያስመዘገቡ አትሌቶች ክልሉን በመወከል በ41ኛው የጃን ሜዳ ሀገር አቋራጭ ውድድር ይሳተፋሉም ተብሏል።

ዘጋቢ፦ ሀብታሙ ዳኛቸው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ግብፆች አልተስማማንም የሚሉት እኛ የምንፈልገው ካልኾነ ሌሎችን ቢጠቅምም ባይጠቅምም ድርድሩ ይፈርሳል ከሚል ግምት ነው” የውኃ ፖለቲካ ተመራማሪ ያዕቆብ አርሳኖ (ዶ.ር)
Next articleመንግሥት ከ9 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በላይ የነዳጅ ድጎማ ማድረጉን የትራንስፖርትእና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር አስታወቀ።