“በክልሉ አንፃራዊ ሰላም እየመጣ በመኾኑ ሥራዎቻችንን ከፌደራል፣ ከዞኖች እና ከወረዳዎች ጋር አጠናክረን እየሠራን ነው” አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር)

52

ባሕር ዳር: ታኅሳሥ 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የፌደራል የከተማና መሠረተ ልማት ሚንስቴር በ2015 ዓ.ም አፈፃፀሞችና የ2016 ቀጣይ ዕቅድ እንዲሁም የአማራ ክልል የ2016 ዓ.ም የአራት ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተካሂዷል።

በውይይቱ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የከተሞች ልማት ዘርፍ አስተባባሪ እና የከተማ እና መሰረተ ልማት ቢሮ ኀላፊ አሕመዲን ሙሐመድ (ዶ.ር) ፣ የከተማና መሠረተ ልማት ሚንስቴር ሚንስትር ዴኤታ አቶ ፈንታ ደጀን፣ የክልሉ የተለያዩ ቢሮ ኃላፊዎች እና ከንቲባዎች እንዲሁም የሚንስትር መሥሪያ ቤቱና የክልሉ ቢሮ የየዘርፍ ኃላፊዎች ተገኝተዋል

ዶክተር አሕመዲን ምንም እንኳ በአማራ ክልል ተፈጥሮ በቆየው የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት ሥራዎቻችንን በተገቢው ፍጥነት ለማጠናቀቅ እንቅፋት ቢኾንብንም አቅም በፈቀደ መጠን ለመሥራት ጥረት አድርገናል ብለዋል ።

በተለይ ደግሞ አሁን ላይ በክልሉ አንፃራዊ ሰላም እየመጣ በመኾኑ ሥራዎቻችንን ከፌደራል፣ ከዞኖች እና ከወረዳዎች ጋር አጠናክረን እየሠራን እንገኛለን ብለዋል።
አቶ ፈንታ ደጀን በበኩላቸው ከተሞች የኢኮኖሚና ማኅበራዊ ዕድገት ማንቀሳቀሻ ዋና ሞተር ናቸው ብለዋል።

በሀገራችንም አዳዲስ ከተሞች በመቆርቆር እና ወደ ጎን በመስፋፋት ሰፊ የኢኮኖሚ ምጣኔ እየተካሄደ እንደኾነም ጠቅሰዋል። የዕድገት ምጣኔዉን በአግባቡ ከተጠቀምንበት መልካም አጋጣሚ ካልተጠቀምንበት ደግሞ ውድቀት መኾን እንደሚችል ገልጸዋል ።

በውይይቱ የፌደራል የከተማና መሠረተ ልማት ሚንስቴር የ2015 ዓ.ም አፈጻጸምና የቀጣይ የ2016 ዓ.ም ቀርቧል። የአማራ ክልል የ2016 ዓ.ም የአራት ወራት አፈጻጸምም ቀርቧል። በቀረቡት ሰነዶች ዙሪያም ውይይት ተካሂዷል። ይህ የውይይት መድረክ በቀጣይ ቀንም በልምድ ልውውጥና በሌሎች ፕሮግራሞች እንደሚቀጥል ከክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleማኅበረሰቡን በቅንነት ለማገልገል መዘጋጀታቸውን የሰሜን ጎንደር ዞን የመንግሥት ሠራተኞች ተናገሩ።
Next article‘በአዳማ ያየነውን ተሞክሮ በአማራ ክልል በስምንት ከተሞች ተግባራዊ ለማድረግ ይረዳናል” ዶክተር አሕመዲን መሐመድ